የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...